በአራዳ ክ/ከተማ የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ት/ቤት ውስጥ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የሻይ ክበብ ወይም ካፌ ያልተሟሉ እቃዎችን ማሟላት የሚችሉ በተጨማሪም የሻይ ክበብ የሚስፈልገውን ማሟላት የሚችሉ እና ስራውን በጥራት በመስራት የሻይ ቤት ክበብ ልምድ ያለው /ያላት/ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ት/ቤት ውስጥ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የሻይ ክበብ ወይም ካፌ ያልተሟሉ እቃዎችን ማሟላት የሚችሉ በተጨማሪም የሻይ ክበብ የሚስፈልገውን ማሟላት የሚችሉ እና ስራውን በጥራት በመስራት የሻይ ቤት ክበብ ልምድ ያለው /ያላት/ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ ት/ቤቱ ይጋብዛል።
- በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑንና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎትን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- የሻይ ማፍሊያ ማሽን ማቅረብ የሚችል /የምትችል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ትቤት በመቅረብ መውሰድ የሚችሉና የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ቢሮ ቁ. 08 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በሲፒአ ከማረጋገጫ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጤና ምርመራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ. 08 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በት/ቤቱ የሻይ ቤት ከኪራይ ነፃ ፤ የመብራትና የውሃ ክፍያ በነፃ እንደሚሆን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች በት/ቤቱ የሻይ ክበብ በአካል በመቅረብ ማየት የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት የሻይ ክበብ ውስጥ የሰራ የሰራች/ እና በተጨማሪም በማንኛውም የስራ ሰዓት ሰራተኞች መጠቀም የሚችሉ መሆን አለበት።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ቀይ ኮከብ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሃንስ ቤተክርስትያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-71-50-64 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የቀይ ኮከብ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
