Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ 2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ 2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  2. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  3. የሠራተኞች የድንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቆች
  4. ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መፅሐፍት
  5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  6. ቋሚ እቃዎች

በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸሁ።
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ።
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባችኋል።
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ለውል ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) 10% ዋስትና ማቅረብ የሚችል
  8. የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ) የማይመለስ በመክፈል መግዛት የሚችል
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።
  10. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ቫትን ጨምሮ ተሞልቶ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO) ደግሞ በጨረታው አርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚመጡ ነጋዴዎች የተሰማሩበትን ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በት/ቤቱ ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርበታል።
  13. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ተዘግቶ በዚያው እለት 4:30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
  14. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ከንግድ ማተሚያ ጀርባ (ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አሮጌው ቄራ በሚወስደው መንገድ በሜሪስቶፕስ ትንሽ ገባ ብሎ)።

ስልክ ቁጥር፡- 0118548084

 

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender