በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የተለያዩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ክፈለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenu Bureau Arada Sub City Small Tax Payers Branch Office) - 001/2018
ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ፡
ሎት 1፡- ደንብ ልብስ
ሎት 2፡- የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች
ሎት 3፡- ህትመት
ሎት 4፡- የጽዳት እቃዎች
ሎት 5፡- የተሽከርካሪ ጎማና የመኪና ጌጣጌጥ
ሎት 6:- የታሸገ ውሃ
ሎት 7፡- የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች
ሎት 8፡- የቢሮ ፈርኒቸር
ሎት 9፡- የጀነሬተር ጥገና
ሎት 10፡- በውል የሚፈጸሙ የሙያ አገልግሎት ግዥ
ሎት 11፡- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፤ ፎቶኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር ለጥገና አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች በ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /TIN/ ያላቸው መሆኑን፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የዕቃዎችን ዝርዝር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ለተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤
- ከሎት አንድ እስከ ስድስት ድረስ የምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 2 ሲሆን “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ” እንዲሁም ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ግዴታ ነው። ሎት ሰባት እና ሎት አስር ለምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 4 ቴክኒካል ሰነድ “አንድ አርጅናል እና ኮፒ” በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ሎት የፋይናንሻል የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ” በድምሩ ሁለት ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት በየሎቱ በመፃፍ በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎኘ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ፒያሳ እናት ህንፃ በአራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ታሽጐ ልክ ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው የብር መጠን ሰንጠረዥ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን |
|
1 |
ደንብ ልብስ |
5,812.56 |
|
2 |
የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች |
41,274.4 |
|
3 |
ህትመት |
62,597 |
|
4 |
የጽዳት እቃዎች |
13,355.6 |
|
5 |
የመኪና ዕቃ |
2,000 |
|
6 |
የታሸገ ውሃ |
10,800 |
|
7 |
የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች |
21,208 |
|
8 |
የቢሮ ፈርኒቸር |
40,200 |
|
9 |
የጀነሬተር ጥገና |
20,000 |
|
10 |
የጽዳት አገልግሎት ሰራተኞች ከነ ሙሉ የማፅጃ መሳሪያዎች እና የፅዳት እቃ |
10,000 |
|
11 |
የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር ለጥገና አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች |
10,000 |
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ /ቫት/ በፊት መሆኑን ገልጸው መፃፍ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለጸ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ለተጫረተበት ዕቃ ናሙና ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ከጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስረከብ ይኖርበታል፤
- ጽ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-126-52-95 ወይም 011-126-55-17 መጠየቅ ይቻላል ።
ማሳሰቢያ
- ለጽዳት አገልግሎት ስራ የሚያስፈልጉ የማጽጃ መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች አሸናፊው ድርጅት ያቀርባል።
- ለጽዳት ሰራተኞች ለጽዳት አገልግሎቱ ስራ የሚያስፈልጋቸውን የስራ ልብስ ወይም የደንብ ልብስ በአሸናፊው ድርጅት ይሸፈናል።
- የጽዳት አገልግሎቱ የሚከናወነው በመንግስት የስራ ቀናትና ሰአት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በየቀኑ 8:00 ሰአት እና ቅዳሜ 8:00 ሰአት ነው። (እሁድንና የበአላቶች ቀናትን አይጨምርም)።
- አሸናፊው ድርጅት የቅ/ጽ/ቤቱን ህግ የሚያከብር መሆን አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት ከመ/ቤታችን ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል የመዋዋል ግዴታ አለበት።
- የጽዳት አገልግሎቱ የሚከናወንባቸው ከGround/ ምድር ቤት ጀምሮ እስከ 5ኛ ፎቅ ድረስ የተከራየባቸውን ክፍሎችና የቢሮ ዕቃዎች፣ መስኮቶች እና ክፍሎችን ለመለየት የተሰሩ የአልሚኒየም መስታወቶች፣ ኮሪደሮችንና መጸዳጃ ቤቶችን ጭምር ነው፡፡ 4ኛ ኮሪደሮችና መፀዳጃ ቤት እና 5ኛ ፎቅ ኮሪደሮች በህንፃው ባለቤት የሚፀዱ ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
