Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማ/ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ የግንባታ ዕቃዎችን፣ አላቂ የፅህፈት እና የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት እና ጨርታ ጨርቅ፡- በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል/ጨ/001/2018

 

በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማ/ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ የግንባታ ዕቃዎችን፣ አላቂ የፅህፈት እና የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት እና ጨርታ ጨርቅ፡- በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
  3. እሸናፊ ድርጅት ባሸነፋቸው እቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ማቆየት ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃውን ሙሉ ሥም የተሰራበትን ሀገርና የጥራት ደረጀውን /Specification/ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መግለፅ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር፡-
    • ለሎት 1 አልባሳት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር /
    • ለሎት 2 የፅህፈት ዕቃዎች ብር 35,000 /ሰሳሳ አምስት ሺህ ብር/
    • ለሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች ብር 140,000/ አንድ መቶ አርባ ሺህ ብር/
    • ለሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት (ሲ.ፒ.አ) CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
  7. በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ቢሮ ውስጥ በሚገኘው ሚኒ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ጨረታው በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡10 ይከፈታል።
  8. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን የማጓጓዝ ትራንስፖርት /ወጭ በራሱ በመሸፈን ከሀዋሳ በስተ ደቡብ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል።
  10. ማሠልጠኛ ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462200033 /0462280001/2 ይደውሉ!

 

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ

 

Save Tender