Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ኡራ ወረዳ : ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-17-89-92-80
  • Website
  • Deadline13 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-13 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Vehicle tire

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሞተር ሳይክልና ደንብ ልብስ እንዲሁም የመኪና ጎማዎች በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኡራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሞተር ሳይክልና ደንብ ልብስ እንዲሁም የመኪና ጎማዎች በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
  2. የዘመኑ ግብር የከፈለ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
  5. የጨረታውን ሠነድ በ 17/1/2018 ዓ.ም
  6. ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሠዓት ድረስ በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
  9. የገዙትን የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ5 ቀን በኋላ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 3/2/2018 ዓ.ም ይከፈታል ዕለቱ የእረፍት ቀን አሊያም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ ንብረቶቹን የሚያስረከቡበት ቦታ በቤ/ጉ/ክ/መ/ ኡራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ይሆናል።
  12. ተጫራቾች ዋናው /ኦርጅናል/ማስረጃ 1 /አንድ/ ኮፒ እና በተጨማሪ 2 /ሁለት/ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች የታሸጉ በድምሩ 3 /ሶስት በማድረግ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ ሊሆኑ የሚችለው በነጠላም ሆነ በዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የጨረታው አሸናፊ ሊያደርግ ይችላል፡፡
  14. ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ማህተም ተመትቶ አብሮ መመለስ አለበት፡፡
  15. ማሳሰቢያ:- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ናሙናው ኮሚቴው በድርጅቱ ሄዶ ማየት አለበት፡፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ተጫራቾች በጨረታው ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-17-89-92-80/ 0925821115

 

የኡራ ወ/ግዥና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት

 

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE