Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን ዕቃዎች በአንደኛ ዙር በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን ዕቃዎች በአንደኛ ዙር በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት1፡- የደንብ ልብስ

ሎት2፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት3፡- የፅዳት እቃዎች

ሎት 4፡- የት/ት ዕቃዎች

ሎት5፡- የጥገና ዕቃዎች

ሎት6፡- የቋሚ ዕቃዎች

ሎት7፡- የኮምፒውተር ግዥ (laptop)

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣ የግብር ክሊራንስ፣ በመንግስት እቃና አገልግሎት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የተሰጠ ፈቃድ ሰርትፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ ክ/ሂ/ግ/ንብ/ቡድን መሪ ቢሮ በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ 10 የስራ ቀናት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት1፣2፣3፣4 ናሙናዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የመጻሀፍት ግዥ በፎቶ የተደገፈ ሳምፕል እና የጥገና ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ዕቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ሲጠበቅባችሁ ለሳምፕል ማቅረብ የማይመቹ ዕቃዎች ላይ በፎቶ የተደገፈ ናሙና ማቅረብ ሲጠበቅባቸው ለሎት6 በፎቶ የተደገፈ ምስል እንዲሁም የዕቃዎቹን ማብራሪያ የሚገልፅ መቅረብ አለበት ለሎት7 የተጠቀሰውን ዕቃ ሙሉ ለሙሉ የሚገልፅ የተሟላ ማብራሪያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና በፖስታ በማሸግ ለእቃ ግዥው ለሎት1- 22,000.00 (ሀያ ሁለት ሺ ብር ብቻ) ፣ ለሎት2- 22,000.00 (ሀያ ሁለት ሺ ብር ብቻ) ፣ ለሎት3-20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) ፣ ለሎት4- 16,000.00 (አስራ ስድስት ሺህ ብር ብቻ) ፣ ለሎት5- 5000.00 (አምስት ሺ ብር ብቻ) ለሎት6- 4000.00 (አራት ሺ ብር ብቻ) ፣ ለሎት7- 6000.00 (ስድስት ሺ ብር ብቻ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ያሲያዙት የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ሲፒኦ ይመለስላችኋል፡፡
  5. ተጫራቾች ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዳቸውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁሉም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ ከ/ሂ/ግ/ንብ ቡድን መሪ ቢሮ ይከፈታል። ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ኮተቤ አዋሽ ባንክ ፊት ለፊት ባለው አስፋልት መንገድ ገባ ብሎ (መምህራን ኮሌጅ በስተጀርባ) በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ

ስ.ቁ 0118 68 40 22 ወይም 0118 68 40 21

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender