በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የመኪና ጎማ፣ የምግብ መስተንግዶ፣ የባሕል አልባሳት፣ የመጽሐፍ ሕትመት፣ የሞተር ሣይከል ግዥ፣ የጽ/ መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ተጫራቾች ( በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደ/ኢ/ክልል አሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የመኪና ጎማ፣ የምግብ መስተንግዶ፣ የባሕል አልባሳት፣ የመጽሐፍ ሕትመት፣ የሞተር ሣይከል ግዥ፣ የጽ/ መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ተጫራቾች ( በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ - የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፈቃድ ያሳደሱ፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN Number) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፊኬት (VAT) ማስረጃ ያላቸው፣ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፡ የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፡ የመኪና ጎማ 10,000 ብር፤ የባሕል አልባሳት 10,000 ብር፣ የመጽሐፍ ሕትመት 1,000 ብር፣ የጽ/ መሣሪያ 5,000 ብር፤ የጽዳት ዕቃዎች 3,000 ብር ለሞተር ሳይክል ግዥ 20,000 ብር እና የኤሌክትሮኒክስ 20,000 ብር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ከላይ የተገለጹትን ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ በነፃ ከአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ4፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት ሰነዱን አንድ አሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደ/ኢ/ክልል አሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
