የሐመር ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የእንስሳት መድኃኒቶችና 100CC ቦክሰር ሞተር ሳይክሎች ግዥ ጨረታ (ሎት 1 እና 2)
በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ፋይናንስና ፕላ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት እቃዎች ፤-
ሎት 1. የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የእንስሳት መድኃኒት ግዥ CPO 10,000 /አሥር ሺህ ብር)
ሎት 2 የሐመር ወረዳ ሴክቴር መ/ቤቶች ቦክሰር ሞተር ሳይክል 100 ሲሲ CPO 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ CPO /በጥሬ/ የጨረታ ማስከበሪያ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል :: ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል ::
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ ማለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት VAT ተመዝጋቢ መሆኑን እንዲሁም ግብር የከፈለበትን ማስረጃ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ::
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ሰርተፍኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው::
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ለሐ/ወ/ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በሐመር ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የግዥ ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው /አሥራ ስድስተኛ/ የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ይከፈታል ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6፡ 30 ለዚህ ስራ የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ::
- ጨረታው በዚህ ዕለት በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል :: ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም ::
ማሳሰቢያ ፤- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው ::ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል :: የጨረታ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ እቃውን ወደ ወረዳ ማእከል ማድረስ ይጠበቅበታል ::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913893126/ ወይም 0916856359 / 0916412104
በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ፋይናንስና ፕላ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Hammer woreda Finance and Plan Office seeks bidders for Lot 1 veterinary medicines (for the Agriculture Office) and Lot 2 100cc boxer motorcycles (for sector offices), via national open tender. Eligible bidders need a valid trade license, tax compliance, TIN, VAT registration, and supplier registration.
