Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ የጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተዘረዘሩ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


 

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ቁጥር ጉሆ 01/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ የጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተዘረዘሩ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ሎት 1 የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  2. ሎት 2 የተለያዩ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  3. ሎት 3 የተለያዩ የደንብ ልብስ እና ጨርቆች
  4. ሎት 5 የተለያዩ የህንፃ መሳሪያዎችና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያሳደሳችሁ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  3. በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 4000.00 /አራት ሺህ ብር/ ለሎት 2 ብር 4000.00 /አራት ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 4 ብር 4000.00 /አራት ሺህ ብር/ ለሎት 5 ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ በCPO በጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስም ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች አሸናፈ የሆኑባቸው ዕቃዎች ከሆስፒታሉ መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 27/1/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዢ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 51 መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ወስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ በCPO የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
  8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ወስጥ የውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ ሆስፒታሉ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
  9. ተጫራቾች ለሎት 03 እና ለሎት 04 ከጨረታ ሰነዱ ጋር ናሙና/ሳምፕል አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 27/1/18 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት በቀን 27/1/2018 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሆስፒታል ግዢ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 51 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራቶች የተጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና ሳምፕል/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 03320514 ፤ 03320515 ይደውሉ

 

ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

Save Tender