Tender Detail

Tender Details


በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን አወዳድሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-001/18

 

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ማለትም፡-

ሎት1 የደንብ ልብስ፣

ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት3 አላቂ የህክምና እቃዎች

ሎት4 አላቂ የት/እቃዎች

ሎት5 የጽዳት እቃዎች

ሎት6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መጽሀፍት

ሎት7 ለፕላንት ለማሽነሪ መግዣ

ሎት8 ቋሚ እቃዎች

ሎት9 የመብራት ጥገና ፌክላም

ሎት10 የቢሮ ፓርቲሽንና የበር ፍርግርግና መስታወት መግጠም፣

ሎት11 የቢሮ ሴራሚክና ቴራዞ ንጣፍ፣

ሎት12 የውሃ መስመር ዝርጋታ፣

የመሳሰሉትን አወዳድሮ መግዛትም ሆነ ማስጠገን ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ እቃዎች ግዢው ት/ቤት በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፈቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ካራ ቆሬ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11፡30 ሰዓት ለእያንዳዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ግዢ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ት/ቤቱ ሌላ እማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
  7. ጥቃቅንና አንስተኛ የሚያመጡት ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ብር 10,000 ብር፣ ለሎት 2 ብር 4,000፣ ለሎት 3 ብር 1,000፣ ለሎት 4 ብር 3,000፤ ለሎት 5 ብር 4,000፣ ለሎት 6 ብር 6,000፣ ለሎት 7 ብር 4,000፣ ለሎት 8 ብር 4,000፣ ለሎት 9 ብር 3,000፣ ለሎት 10 ብር 5,000፣ ሎት 11 ብር 5,000፣ ሎት 12 ብር 5,000 የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ /cpo/ በተረጋገጠ ቼክ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. የቋሚ እቃዎችን መስሪያ ቤቱ ድረስ ሳምፕል ማምጣት የማይችሉትን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሽ ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቱ ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ ኮንዶሚኒየም ወይም ቢቂላ መናፈሻ ጀርባ

ስልክ ቁጥር፡- 0912120394/093776785

 

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender