የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 የበጀት ዓ.ም ግዢ በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ እስቴሽነሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን እና የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 የበጀት ዓ.ም ግዢ በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ እስቴሽነሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን እና የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- ወቅታዊ የግብር ግዴታውን ያሟሉ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ
- ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ቲን ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃለይ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ስለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የበረክ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሂሳብ ቁጥር 1000065445925 በመክፈል ሰነዱን ከበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት በመግዛት በጨረታው መካፈል ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው ለ15 የስራ ቀን በተከታታይ ቀን አየር ላይ ውሎ በ16 ኛው በስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማንኛውንም ወጪ ችሎ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ፍ/ቤት ድረስ ያቀርባል፤ ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0116860263/ 0988687829
የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት
