በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ግቢ ውስጥ በሚገኝ ካፌ የውስጥ መስተንግዶ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ግቢ ውስጥ በሚገኝ ካፌ የውስጥ መስተንግዶ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በካፌ ውስጥ የሚሰጡ ድጋፍ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከኪራይ ነፃ የካፌ ቤት፣ የውሃ፣ የተወሰኑ የኩሽና እቃዎች፣ ወንበርና ጠረጴዛ እንዲሁም ቴሌቪዥን አንድ እና ፍሪጅ አንድ ያለው ሲሆን በዚህ ላይ አጠናክሮ መስራት የሚፈልግ ተወዳዳሪ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት (VAT) የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናስ ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በCPO ማስያዝ የሚችሉ፤
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ያሸነፈው ተጫራች ደረጃቸውን የጠበቀ መስተንግዶ እና የሚደረጉ ድጋፎችን ታሳቢ ያደረገ ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በ11ኛው የሥራ ቀን በ3፡30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል፡፡ በዛው እለት የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ በካፌው ውስጥ ለሚገኙ ንብረቶች ተመጣጣኝ ዋስ ማቅረብ የሚችል በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የመስተንግዶ አይነቶችን በፎቶ ከነሰዱ ጋር በዝርዝር እንድታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-67-85-56 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- የተባበሩት አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ወደ አይሲኤምሲ ሆስፒታል መሄጃ መንገድ ላይ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
