የካ ተራራ ቅድመ አንደኛ፡ እንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት ከዚህ በታቸ በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች 1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የካ ተራራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2018
የካ ተራራ ቅድመ አንደኛ፡ እንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት ከዚህ በታቸ በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች 1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
የሎት ቁጥር |
የእቃው አይነት |
|
ሎት 1 |
ደንብ ልብስ |
|
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
|
ሎት 3 |
ህትመት |
|
ሎት 4 |
የህክምና እቃ |
|
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት |
|
ሎት 6 |
የጽዳት እቃዎች |
|
ሎት 7 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እቃዎች |
|
ሎት 8 |
ቋሚ የኮምፒውተር ጥገና እና ሰርቪስ |
|
ሎት 10 |
ቋሚ የቢሮ እቃ (ፕላንትና ማሽነሪ ግዥ) |
|
ሎት 11 |
ቋሚ የቢሮ እቃ (የህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ግዥ) |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ናሙና በሚያስፈልጋቸው እቃዎች የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና በዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስረከቢያ ጠቅላላ ዋጋ፡-
- ሎት 1 ደንብ ልብስ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 3 ህትመት 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት 4 የህክምና እቃ 3000.00 (ሦስት ሺህ ብር)
- ሎት 5 አላቂ የትምህርት እታ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 6 የጽዳት እቃዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እቃዎች 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 8 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገና እና ሰርቪስ
- ሎት 10 ቋሚ የቢሮ እቃ (ፕላንትና ማሽነሪ ግዥ) 5000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 11 ቋሚ የቢሮ እቃ (የህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ግዥ) 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና በጨረታ ስራ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ሰነድ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና አርጅናል የካ ተራራ ቅድመ እንደኛ፣ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየካ ተራራ ቅ/አ/አ/መ ደረጃ ት/ቤት ላይ በላይብረሪ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውን የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዢ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡
- ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- መገናኛ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ ቤል ቪው ሆቴል ፊት ለፊት ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-13-94-98-86 / 251-11-66-05-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የካ ተራራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
