የቦሌ አዲስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበልን መደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ ድጎማ በጀት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳር ወረዳ 09 ት/ጽ/ቤት ቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ /ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- 001/2017
የቦሌ አዲስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበልን መደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ ድጎማ በጀት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የዕቃው ዝርዝር (ዓይነት) |
|
1 |
ሎት 1 |
የስፖርት መምህራን የስፖርት ቱታና ጫማ እንዲሁም የሠራተኞች የደንብ ልብስ |
|
2 |
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ (የጽህፈት) መሳሪያዎች |
|
3 |
ሎት 3 |
አላቂ የህክምና እቃዎች (የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫን ጨምሮ) |
|
4 |
ሎት 4 |
አላቂ የትምህርት ማበልጸጊያ (የማእከል) የቤተ-ሙከራና የስፖርት እቃዎች እንዲሁም የቧንቧና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች |
|
5 |
ሎት 5 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
|
6 |
ሎት 6 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
|
7 |
ሎት 7 |
የጥገና የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ እቃዎች |
|
8 |
ሎት 8 |
ቋሚ እቃ እና ለህንጻ አገልግሎት የጥገና እቃዎች |
ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ከድረ-ገጽ ላይ የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙና በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ዋስትና እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከት/ቤቱ የ/ከ/ፋ/ግ/ን/ አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በሎት ቁጥር 7 ለተጠቀሱት ስራዎች ተጫራቾች በቦታው ተገኝታችሁ ዝርዝር መረጃ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ ማግኘት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የለባቸውም።
- ተጫራቾች ያላቸውን መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በት/ቤቱ ፋ/ግ/አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው 10ኛው ቀን ከተጠናቀ በኋላ ባለው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ለሆኑባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ ብር 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ለጨረታው ባወጣው ጠቅላላ ዋጋ 20% ከፍ ወይም ዝቅ ብሎ የግዢ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ለመሳተፍ መሞከር በህግ ያስቀጣል።
ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በአካል ት/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ያነጋግሩን።
አድራሻ፡- ሲኤምሲ አልታድ ሚካኤል ከመስጊድ ወረድ ብሎ ፊጋ መብራቱ ጋር ሲደርሱ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ከቦሌ አዲስ የመጀ/ደ/ት/ቤት አጠገብ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ :- 011-6-59-60-90 / 011-6-59-60-61
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
