Tender Detail

Tender Details


በብልጽግና ፓርቲ የማ/ኢ/ክ/ቅ/ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከፍተኛ ጥራት ያላቸው Desktop Computer Printer, Laptop Photo Copy Machine የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የጽሕፈት መሣሪዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የማ/ኢ/ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በብልጽግና ፓርቲ የማ/ኢ/ክ/ቅ/ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከፍተኛ ጥራት ያላቸው Desktop Computer Printer, Laptop Photo Copy Machine፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የጽሕፈት መሣሪዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች፡
    1. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላችሁና የሰነዱን ኮፒውን ማቅረብ የምትችሉ፣
    2. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማቅረብ
    3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላችሁና የሰነዱን ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፤
    4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላችሁና ኮፒ ሰነዱን ማቅረብ የምትችሉ፤
    5. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላችሁና እና ኮፒ ሰነዱን ማቅረብ የምትችሉ፤
    6. የ2016/2017 ዓ.ም የመልካም የሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ ሁሉ ቅ/ጽ/ቤቱ ለግዥው ጋብዟል፣
  2. አቅራቢዎች:
    1. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነዱ (Bid Bond) ብር 50,000 በባንከ በተመሰከረለት (CPO) ከነማስከበሪያው ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    2. ተጫራቾች የግዥ ጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ/ Bid Document / የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በማ/ኢ/ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ክፍል 1ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
    3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ መወዳደሪያ ኮፒ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ኢ/ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የፋ/ን/ሰ/ሀ/አስተዳደር መምሪያ ግዥ ከፍል ቀርበው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
    4.  ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ሥራ ቀን 4፡00 ለተጫራቾች ክፍት በመሆን በዚያው ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በዕለቱ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
    5.  የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
    6.  ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 0967285336/0993425904

 

የማ/ኢ/ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

ሆሳዕና

 

Save Tender