Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline07 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-07 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Hotel Service Provision

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የምግብ ደህንነት አስተዳደር ስርዓት (Food Safety Management System ISO 22000:2018) የመልሶ ማረጋገጫ አገልግሎት አቅራቢ የሆኑ የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለኢን-ፍላይት ኬተሪንግ አገልግሎት ክፍል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T- 574

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የምግብ ደህንነት አስተዳደር ስርዓት (Food Safety Management System ISO 22000:2018) የመልሶ ማረጋገጫ አገልግሎት አቅራቢ የሆኑ የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለኢን-ፍላይት ኬተሪንግ አገልግሎት ክፍል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጨረታ ቁጥር SSNT-T-574 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ150 ቀናት ይቆያል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው። አሸናፊው ተጫራች የማሸነፊያውን ማስታወቂያ ከተቀበለ በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር አለበት፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 27 ቀን 2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል

ስልክ ቁጥር፡- 011-5-17-49-18

ኢ-ሜይል:- Assefah@ethioplanairlines.com

አቶ አሰፋ ሀይሉ

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE