የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የ17/20 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 17/20 ጤና ጣቢያ
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/18
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የ17/20 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር/ የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ/በኢትዮ.ብር |
|
ሎት 1. ቋሚ እቃ |
ብር 10,000 ብር |
|
ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች |
ብር 5,000 |
|
ሎት 3. የደንብ ልብስ |
ብር 5,000 |
|
ሎት 4. የተለያዩ ህትመቶች |
ብር 3,000 |
|
ሎት 5. አላቂ የጽዳት እቃ |
ብር 5,000 |
|
ሎት 6. የኔትወርክ እቃዎች |
ብር 2,000 |
|
ሎት 7. የውሃና የመብራት መፍቻዎች፤ |
ብር 2,000 |
|
ሎት 8. የጀነሬተር ሰርቪስ እና አውቶማቲክ ማድረግ ላውንደሪ ማሽን ሰርቪስና ጥገና የተለያዩ ክፍሎች የአሉሙኒየም ፓርቲሽን ስራና የአጥር ጥገና ስራ |
ብር 5,000 |
|
ሎት 9. ቋሚ የህክምና እቃ |
ብር 10,000 |
|
ሎት 10. መድኃኒት እና የላብራቶሪ ሬጀንት |
ብር 10,000 |
|
ሎት 11. የመኪና ኮንትራት ፒካፕ ፤ ላዳ ፤ ሚኒባስ ፤ መካከለኛ አይሱዚ |
ብር 2,000 |
ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 57 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በቢሮ ቁጥር 56 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መስረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቢሮ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ሩዋንዳ ጃፓን ኤምባሲ ገባ ብሎ ወረዳ 02 አጠገብ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር:- 011-6-68-72-98
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 17/20 ጤና ጣቢያ
