Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /Furniture's/፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ ለአንድ የበጀት ዓመት ከሚያቀርብ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /Furniture's/፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ ለአንድ የበጀት ዓመት ከሚያቀርብ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሰረት-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በየንግድ ዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃዳቸውን ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበትን እና የንግድ ፈቃድ ያሳደሱበትን በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ከፍላችን ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለጨረታው ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦርጂናል ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናዎች ላይ በግልጽ በሚታይ የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ እቃ ላይ በማሳረፍ ማቅረብ አለበት።
  5. ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት /15/ ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ብቻ ነው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) የጨረታ ዓይነቱን በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናሉን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የመጨረሻ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥኖች ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ ስድስተኛው የመንግስት የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ላይ በቦሬ ወረዳ አስተዳደር ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  8. ይህ ጨረታ የሚከፈትበት ዕለት በህዝብ በዓላት ካሌንደር የሚዘጋውና ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  9. ተጫራቾች ከሙስናና ከማጭበርበር ተግባር ነጻ ስለመሆናቸውና በፌዴራልና በክልል መንግሰታት ህግ ለማክበራቸው ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ ያለውን ቅጽ መፈረም አለባቸው።
  10. የጨረታው አሸናፊ በግልጽ ማስታወቂያ ወይም በጽሁፍ ደብዳቤ ከተገለጸለት ዕለት አንስቶ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸነፉባቸው ዕቃዎች ዋጋ 10% የጨረታ ውል ማስከበሪያ በኢንሹራንስ ጋራንቲ የተመሰከረ ቼክ / Check / ወይም ጥሬ ገንዘብ አስይዞ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል የመፈራረም ግዴታ አለበት፡፡ ይህንን ባይፈጽሙ መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ያደርጋል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ድርጅት በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለጸለትና ከመ/ቤቱ ጋር ውል ከተፈራረመ በኋላ ዕቃዎቹን በተፈለገው ብዛትና ጥራት መሰረት እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 046-6-67-02-61/ 046-6-67-00-23 ወይም 046-6-67-01-37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender