Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ዝርዝር

ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያ                        ሎት-5 አላቂ ዕቃዎች

ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች                          ሎት-6 ቋሚ ዕቃዎች

ሎት-3 የደንብ ልብስ                            ሎት 7 የዘር ግብዓቶች

ሎት-4 የተሽከርካሪ ጎማ                         ሎት 8 መድረክ ማስዋብ

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው በግልጽ ጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በንግድ ምዝገባ የተመዘገቡና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለ መሆናቸው የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ (2) ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያ -10,000                                ሎት-5 አላቂ ዕቃዎች-10,000

ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች-15,000                                    ሎት-6 ቋሚ ዕቃዎች-20,000

ሎት-3 የደንብ ልብስ -7,000                                        ሎት-7 የዘር ግብዓቶች-5000

ሎት-4 የተሽርካሪ ጎማ-5,000                                       ሎት-8 መድረክ ማስዋብ-2,000

  1. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ከውሃ ልማት ጎን በሚገኘው ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ (200.00) ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ በኤንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታው መክፈቻ ቀን በ11ኛው ቀን ሆኖ ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ጽ/ቤቱ ባቀረበው መጠን ወይም ብዛት ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ አምራች የሆነ ብቻ ሲሆን አምራች መሆኑና የሚያመርተው ዕቃ ተጠቅሶ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ሞዴል መሰረት ብቻ ነው።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ዕቃ (ናሙና ላይ የተለየ ምልክት ወይም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የተከለከለ ነው) አድርጎ ቢገኝ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡ ማንኛውም ተጫራች ማህተሙን የሚጠቀመው በወረቀት ላይ ማህተም በማድረግ ዕቃው ላይ በፕላስተር በመለጠፍ ብቻ ነው።
  11. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም እና የሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበት ዕቃ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርትና ሰራተኛ በማውረድና በማጓጓዝ ባቀረበው ናሙና መሰረት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  13. ለሚገቡ የቋሚ ዕቃዎች እና ቀለሞች ለአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ሰነዱን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  15. ስርዝ ድልዝ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዲሁም ለአንድ ዕቃ ከአንድ ዋጋ በላይ ማቅረብ አይፈቀድም።

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ውሃ ልማት አጠገብ የወረዳው ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንሰ ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913382003/0923286082/0923481386

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender