Tender Detail

Tender Details


የአዳማ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳችን የሚያስፈልጉትን የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር እና የትምህርት መገልገያ መሳሪያዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


                                                                                    የጨረታ ማስታወቂያ

 የአዳማ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳችን የሚያስፈልጉትን የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር እና የትምህርት መገልገያ መሳሪያዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎችን ማቅረብ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ

 * የታደሰ የዘመኑን የንግድ ፍቃድ የ2017/18 ዓ.ም ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡ 

* ተጫራቾች የቫት(ቲኦቲ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

* ተጫራቾች የአቅራቢዎች ተርታ ላይ መመዝገባቸውን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፡፡

 * ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የተወዳዳሪ መመሪያ ላይ የተጠቀሰ ብር/በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡

 * አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን ለአዳማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ አስፈላጊ ወጪውን (የማውረጃ) ይሸፍናል፡፡ * አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡

 * መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይችልም፡፡ * አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡

 * ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሰነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ አለባቸው፡፡

 * ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ) በመክፈል ከአዳማ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 

 * ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት በ8፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 

* መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ 

* ለተጨማሪ መረጃ የአዳማ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት፡፡

 የስልክ ቁጥር 0221127908 ወይም 0221112169 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

                                                  የአዳማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

Save Tender