የአብክመ የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቢሮ ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር፣ አላቂ የቢሮ፣ የጽዳትና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
የአብክመ የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር እቃዎችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽዳት እቃዎችን እና የተሽከርካሪ የቅባትና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ አግባብነት ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
- የግዥ መጠኑ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በግብር አመቱ ተገቢውን ታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር ቀናት/ ቀን ከቀኑ 11:30 ድረስ አራት ኪሎ በሚገኘው አልማ ህንፃ (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከሚገኝበት ህንጻ) ሁለተኛ ፎቅ የአብክመ የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 218 በመምጣት ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የቴክኒክ እና የፋይናንስ ለሚያስፈልጋቸው የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል:: 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል::
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል:: ሲፒኦውን ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የሚፈለጉት ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን::
ማሣሠቢያ:- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-111-26-53-87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
የአብክመ የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
The Amhara Region Intergovernmental Relations and External Affairs Coordination Commission (Addis Ababa office) seeks suppliers of office electronics and furniture, office consumables, cleaning supplies, and vehicle lubricants and spare parts. Licensed bidders with TIN and tax clearance. Open bid.
