በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚውል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፋይናንስ 01/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚውል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያ (ስቴሽነሪ)
ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 3. ፈርኒቸር
ሎት 4. ሞተር ሳይክል
ሎት 5. ሴሌክት ማቴሪያል ሪዳሽ
ሎት 6. መስተንግዶ (ሪፍሬሽመንት)
ሎት 7. ህትመት
ሎት 8. የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች
ሎት 9. የደንብ ልብስ
- ሕጋዊ የሆነ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶችን በግልጽ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዚህም መሰረት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የሥራ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመወዳደሪያ የቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል፣ አንድ ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል አንድ አንድ ኦርጅናል የያዘ አንድ ኮፒ በእናት ኢንቨሎፕ በማድረግ በሰም በማሸግ በእናት ፖስታው ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ሙሉ አድራሻውን በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በእናት ኤንቨሎፑ ላይ መጻፍ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ 5,000 (አምስት ሺ ብር) የኢትዮጵያ ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል ዕለቱ የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ቢያስፈልጋቸው በስልክ 0465560063/0465560853 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠይቅ ይችላሉ፡፡
- ድረ ገጽ www.kulitofinance.org ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
