የኩርፋ ጨሌ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት በሥሩ ባሉት መስሪያ ቤቶች የሚያስፈልጉ ለቢሮ እቃዎች የሚውሉ የቢሮ ቋሚ እቃዎች (ፈርኒቸሮች)፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ እቃዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ የወንድ እና የሴት ጫማዎች፣ ለፅዳት የሚውሉ ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኩርፋ ጨሌ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት በሥሩ ባሉት መስሪያ ቤቶች የሚያስፈልጉ ለቢሮ እቃዎች የሚውሉ ማለትም:-
የቢሮ ቋሚ እቃዎች (ፈርኒቸሮች)፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ እቃዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ የወንድ እና የሴት ጫማዎች፣ ለፅዳት የሚውሉ ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሱትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፦
- የሚፈለግበትን የመንግስት ግብርና ታክስ በሕጉ መሠረት የከፈለና ፍቃዱን ያደሰ
- የግብር ከፋይነት ቁጥር (ቲን) ያላውና የሚያቀርብ የ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የ(VAT) ተመዝጋቢነት መረጃቸው ማቅረብ አለባቸው
- በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ያልታገደ
- የሚያቀርባቸው እቃ ጥራት የታወቀና ለዚህም ከታወቀ የመንግስት መ/ቤት ማስረጃ የሚያቀርብ
- የጨረታ ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ) የኢት.ብር ማስያዝ ይኖርበታል
- ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን እቃ በራሳቸው ወጪ እስከ ወረዳው ንብረት ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ የራሳቸው አርማ እና ማህተብ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በትክክል በመፃፍ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ቀን 22/12/2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 3 እና 4 ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ በዋጋ ማቅረቢያ ኢንቨሎፕ ውስጥ በመክተት አብረው ማሸግ እና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ23/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።
- ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ስረዝ ድልዝ ያለው የማይነበብ የሚያደናግር ሰነድና ማስረጃ ተቀባይነት የለውም
አድራሻችን፡- ምሥ/ሐረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ:- 09 40 59 05 01
ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
