በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የሰራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የሰራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች የጨረታው ሰነድ በአንድ ላይ ተያይዞ ስለሚገኝ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ስለዚህ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና በአቅርቦት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫትና ቲአት (TOT) ተመዝጋቢዎች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴ ይህ ጋዜጣ 01/12/2017 ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ጎሮ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በ6፡00 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ 7፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ አቅራቢዎች የሚቀርቡት እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆንና በሚያቀርቡት የጨረታው ሰነድ ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ ህጋዊ ማህተምና ፊርማ መስፈር አለበት፡፡ ለሚወዳዳሩበት ዕቃዎች ከተጫራች የሚቀርበው ሰነድ የዕቃውን ዝርዝር ዓይነት ስምና የተመረተበት ሀገር /brandname/ እንዲሁም ዘመን የሚገልፅ ሆኖ የእቃው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃ ላይ 10% ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የሚገኘው በጅማ መስመር ሆኖ በወሊሶ እና ወልቂጤ መሃል ከአ/አ 134ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ስልክ 011-345-01-17 ወይም 011-345-06-26
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
