የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁ. 01/2018
የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ለተጠየት የግዥ ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች እና የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እና ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎችና፤ የጽዳት ዕቃዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 350 (ሦሰት መቶ ሃምሳ ብር) ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000041404004 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ንብረት አስተዳደር ፤ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው መክፈላቸውን እና ጨረታ መሰተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን: ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ለቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የእና የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ) ፤ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) ፤ ለጽዳት ዕቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በበቆጂ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0962278710, 0949379552 ይጠይቁ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
