Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአሰላ ከተማ መስተዳድር የአሰላ ሳጉሬ ከተማ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎቸን በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋበዛል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአሰላ ከተማ መስተዳድር የአሰላ ሳጉሬ ከተማ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


የወጣ የግልጽ ጨረታ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአሰላ ከተማ መስተዳድር የአሰላ ሳጉሬ ከተማ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፦

  1. የተለየዩ የውሃ ቧንቧዎችና መገጣጠሚያዎች፡፡ (ሎት 1)
  2. የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎች፡፡ (ሎት. 2)
  3. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያዎች (ሎት 3
  4. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽዳት ዕቃዎች (ሎት.4)
  5. የሰራተኛ የደንብ ልብሶች: (ሎት. 5)
  1. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ወንበሮች (ሎት, 6)
  1. ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች (ሎት.7)
  2. የተለየዩ የመኪና ጎማዎች (ሎት.8)

በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋበዛል፡፡

  1. ዕቃዎቹን በጥራት˚ ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የአቅርቦት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 10% በቼክ ወይም ሲፒኦ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በንግድ ባንከ አካውንታችን አሰላ ወተር ሰፕላይ ሰርቪስ 1000022711378 በሚለው በመክፈል ዋና ቢሮሯችን የከንቲባ ጽህፈት ቢሮ ጀርባ በሚገኝ ህንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 26 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 7፡30 ሰዓት ተዘገቶ ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አሽናፊው ድርጅት በጽሁፍ ከተገለጸ በኋላ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ በአሰላ ሳጉሬ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለአሰላ ሳጉሬ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. የእቃዎች ርክብከብ የሚካሄደው በአሰላ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል።
  11. የእቃው ብዛት የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ከበጀታችን በላይ የሚሆነውን መቀነስ ወይም መጨመር የምንችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአሰላ ሳጉሬ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅትለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0964649194 / 0962203002

 

የአሰሳ ሳጉሬ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

የጨረታ ማስታወቂያ

Save Tender