የወሊሶ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዘመን የተለያዩ የማስተማሪያ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Woliso Polytechnic College (የወሊሶ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የወሊሶ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዘመን የተለያዩ የማስተማሪያ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የአገል/ ሠራተኞች የሥራ ልብስ፣
- ልዩ ልዩ የቢሮ ዕቃዎችና አነስተኛ መሣሪያዎች፣
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
- አላቂ የትምህርት መሣሪያዎች፣
- የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች ናቸው።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
ሀ/ የዘመኑን ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
ለ/ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ሐ/ ተወዳዳሪዎች የሚፈለገባቸውን የባለቤትነት መረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
መ/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በCPO በቅድሚ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሠ/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናው እና ፎቶ ኮፒውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ረ/ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በኮሌጁ የባንክ አካውንት በማስገባት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ሰ/ የጨረታ ማስታወቂያው በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕስት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል/ ዝገ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
ሸ/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-341-24-95 በመደወል ይጠይቁ፡፡
የወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
