በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የመኪና ጎማዎች የቤት ቆርቆሮ እና ሚስማር ሲሚንቶ ፈርንቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች፤ የቤት ቆርቆሮ እና ሚስማር፤ ሲሚንቶ፤ ፈርንቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ፡-
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ የሚያቀርብ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ባሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር መሠረት ከመ/ቤቱ ጋር የውል ስምምነት መፈራረም ይኖርበታል።
- ተጫራቾች እቃዎቹን ከነ ትራንስፖርት ወጭያቸው የሚሸጡበትን ዋጋና አይነት በመለየት በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-11፡30 ድረስ በሥራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በዚህ ቀን በ5፡00 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሑድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይካሄዳል።
- ተጫራቾች በሚፈልጉትና ማቅረብ በሚችሉበት እቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ሆኖም ለአንድ ዓይነት እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን እቃዎች ደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት የማጓጓዣ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ መቻል ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ አይነት ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0963226105 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመደወል ወይም ደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት እቃ ግዥ ክፍል በግንባር ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
አድራሻ ሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከአ/አ በስተሰሜን 89 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
