የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳ 13 አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ለወረዳ 13 አገልግሎት የሚውል የተለያዩ
- የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ እስቴሽነሪ፣ የደንብ ልብስ፣ የቢሮ ፅዳት እቃዎች፡፡
- ቋሚ እቃዎች፣ ኮምፒተሮች፣ ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ፕሪንተሮች ፣ የፕሪንተር ቀለሞች፣ የቢሮ ወንበሮች፣ የቢሮ ጠረፔዛ፣ ፋይል ካቢኔት ፣ ሸልፍ እና የመኪና ጎማዎች እና የመሳሰሉትን
- መስተንግዶ ህትመት፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ድንኳን ኪራይ ፣ የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት የተለያዩ የቢሮ እቃ ጥገናዎች እና የመሳሰሉትን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- በየግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት (VAT) የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናስ ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በCPO ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሰነድና መረጃ ላይ የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ገፅ ላይ በመምታት እና ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አሽጎ በማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የትኛውም ቦታ ላይ ማህተም ሲጠቀሙ ስም ሲጽፉ የድርጅቱን ስም ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋበትን ደረጃቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በራሳቸው ትራንስፖርት እና ማውረጃ ወጪ የወረዳ 13 ፋ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው መጋዘን ገቢ አድርጎ የማስረከብ ሙሉ ሀላፊነት አለበት፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል። በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ወረዳ 13 ፋይናስ ጽ/ቤት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል እንዲሁም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ ፡፡
- ወረዳው የሚፈልጋቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ኦሪጂናል ዕቃዎች እና የእቃውን ጥራት የሚገልፅ እስፔስፊኬሽን በዝርዝሩ የተጠቀሰውን ዓይነት ዕቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 10% በ/ CPO/ በቅድሚያ መስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጽሕፈት መሳሪያ የጽዳት እቃዎች እና ሌሎችም ናሙና የሚያስፈልጋቸው በዝርዝር ከፊስታል ውጪ በሆነ መያዣ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጥቃቅን አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ ስታመጡ ደብዳቤው በጽ/ቤቱ ኃላፊ ቲተርና ፊርማ ተፈርሞ ማምጣት ግዴታ ነው፡፡
- በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ የዕቃው ብዛት የመቀነስም ሆነ የመጨመርም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116678556 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- የተባበሩት አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ወደ አይሲኤምሲ ሆስፒታል መሄጃ መንገድ ላይ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከኮንፌሽን ጀርባ ይገኛል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
