በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት አመት ለከተማው ኤሌክትሮኒክስ ፣ እስቴሽነሪ ፣ ፈርኒቸር ፣ የውሃ እቃ ፣ ሞተርሳይክል ፣ አልባሳት ፣ የንብ ማነቢያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01/2018
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት አመት ለከተማው ኤሌክትሮኒክስ ፣ እስቴሽነሪ ፣ ፈርኒቸር ፣ የውሃ እቃ ፣ ሞተርሳይክል ፣ አልባሳት ፣ የንብ ማነቢያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተወዳዳሪዎች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ሰነድ በግ/ን/አስ/ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል እስከ 20ኛው ቀን መግዛት ይቻላል፡፡ የጨረታ ዶክመንት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ22 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚያው እለት 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ (cpo) ዋጋ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለፈርኒቸር ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለእስቴሽነሪ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ ለውሃ እቃ ብር 20,000 /ሃያ ሺ/ ለአልባሳት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ለንብ ማነቢያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ የሞተር ሳይክል ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም በማሰራት ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ከ ተራ ቁጥር 1፣2፣3 እና 4 ላይ የተገለፁት ዶክመንቶች / መረጃዎች ዋናው እና ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ የበአል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0113110663/ 0913 76 56 94/ 09 19 85 70 00
በማከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
