Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
  • Address 6ኪሎ ወደ ጃልሜዳ መንገድ በሚወስደው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline12 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-12 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Hotel Service Provision

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል።

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል። ስለዚህ ጨረታውን ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተግልጸው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ፖስታ በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ከቢሯችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1002 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ማቅረብ የሚችሉትን የምግብ ዓይነት ፍርድ ቤቱ ባቀረበው ሰነድ መሰረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
  6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ይሆናል። በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
  8. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ በፅሁፍ ከተገልፀ በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- 6ኪሎ ወደ ጃልሜዳ መንገድ በሚወስደው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት

 

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE