የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ መስሪያ ቤቶች ግልጋሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር ጎማ እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ መስሪያ ቤቶች ግልጋሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር ጎማ እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ንግድ ፍቃድ ከሚፈቅድለት ውጪ መወዳደር አይችልም ፡፡
- በአቅራቢነት መዝገብ መመዝገባቸውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ፡፡
- የተጫራቾች ሙሉ ስም፣ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም የሌለው እንዲሁም በዋጋ አጻጻፍ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጸምላቸው ያሸነፉትን እቃዎች የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት አጠናቀው ገቢ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ 20,000 (ሃያ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ከአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ከሞሉ በኋላ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 14/12/2016 ዓ.ም 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አርሲ ሮቤ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የፌዴራልና የክልሉን አዋጅና ደንቦችን የማክበርና በእቃ አቅራቢነት ወቅት የሚቀርበውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ከሚያቀርበው እቃ ጠቅላላ ዋጋ የሽያጭ ታክስ 2 ፐርሰንት ገቢ ያደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
