የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለነቀምቴ ኮምፕሬንስብ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለነቀምቴ ኮምፕሬንስብ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችዋል።
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት በንግድ ዘርፍ ላይ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ከምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከፎቅ ቁጥር 1 ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቁጥር 13 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ካለፉት ዓመታት በአቅራቢነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪይ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond (CPO) 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንከ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ምግብ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የምግቡን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification” ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋው በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማሰፈርና ማህተም ማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታ ዶከመንታቸውን ኦሪጅናል ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ እና ኮፒውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ትልቅ ፖስታ በ15ኛው ቀን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከ10፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ከሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር የተሰጠውን መመሪያ (መስፈርቶች) በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተያይዞ የቀረበ መመሪያ መከተል አለባቸው።
- የጨረታው ሣጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ አሸነፊ ተጫራቾች ምግብን ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ነቀምቴ በሚገኘው በውል ሰጭው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
- መ/ቤታችን በሚያወዳድረው ጠቅላላ የዋጋ ብዛት ላይ እንደየአሰፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች ምግብ አሸንፊው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማሰከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸነፊ መሆናቸው ከተገለጸ ከአምስት ቀን በኃላ በውል ሰጪው መ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
ስልክ 0576-602-207 / 0576-613-410
የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
