ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት
አንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች፡
|
የሎት ዝርዝር |
የዕቃው አይነት |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
32000 ብር |
|
ሎት 2 |
አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች እና መገልገያ እቃዎች |
29000 ብር |
|
ሎት 3 |
የጽዳት እቃዎች |
49000 ብር |
|
ሎት 4 |
ቋሚ ዕቃ ትልቁ ጄኔሬተር |
50000 ብር |
|
ሎት 5 |
ዲኮር፤ ሞንታርቦ እና ጄኔሬተር ኪራይ |
10000 ብር |
|
ሎት 6 |
ህትመት ስራዎች |
10000 ብር |
|
ሎት 7 |
መስተንግዶ |
3000 ብር |
|
ሎት 8 |
የአትክልት ልማት ዘር |
2000 ብር |
|
ሎት 9 |
የትራንስፖርት አገልግሎት /መኪና ኪራይ/ |
3000 ብር |
|
ሎት 10 |
የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ እና ቁሳቁሶች /ዕቃዎች/ |
3000 ብር |
|
ሎት 11 |
የኮምፒተር ፤ ፕሪንተር፤ ስካነር እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና የፈርኒቸር /ጠረጴዛ፤ ወንበር፤ መሳቢያ የመሳሰሉት / ጥገና |
3000 ብር |
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ግብር የከፈሉበትና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል የንግድ መስክ ያለው።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተረጁ ከሆነ የተደራጁበትን የስራ መስክ /ዘርፍ/ የሚገልጽ በጨረታው የሚያሳትፍ የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊው ፊርማ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ በየሎቱ በብር 250.00 /ሁለት መቶ ሀምሳ ብር/ በመግዛትና በትክክል በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/9 ፋይናስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በሎት 5፣ ሎት 6፣ ሎት 7፣ ሎት 8 ፣ ሎት 9 እና ሎት 11 የቲኦቲ እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ሌሎች ሎቶች ማለትም ሎት1 ፣ ሎት2 ፣ ሎት3 ፣ ሎት4 ፣ ሎት7 የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን እቃ (ሎት 1፣ ሎት 2 ሎት 3 እና ሎት 5 ዲኮር በፎቶ ፣ ሎት6 ሎት 10 ላይ የሞተር ሳይክል እቃዎች ከጎማ ውጪ) ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ናሙና መቅረብ የሌለባቸው ደግሞ ሎት 4 ፣ ሎት 5 ፣ ሎት 7 ፣ ሎት 8 ፣ ሎት 9 ፣ ሎት 10
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን እቃ የቫት ዋጋ ጨምሮ እቃውን ዝርዝር ማስገባት ይኖርበታል።
- ቫትን ያላካተተ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ይሰረዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጽዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ አገር ውስጥ ምርት የሚያቀርቡ ይበረታታሉ።
- የጨረታ አሸነፈው ያሸነፈበት እቃ በሚደረገው ውል መሰረት በራሱ ትራንስፖርት በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግንባር ቀርቦ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ዕለቱ 4፡00 ቢሮ ቁጥር 7 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/9 ፋይናን ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ከቀባው እቃ እስከ 20 ፐርሰንት የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለአሸናፊዎች ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለበት፡፡
አድራሻ፡- ጦርሀይሎች ሙሉ ወንጌል ቸርች ጀርባ ገባ ብሎ
የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 0113-69-19-92
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት
