ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም
|
ተ.ቁ |
ጨረታ የሚወጣው የእቃው ዓይነት |
ሎት |
|
1 |
የደንብ ልብስ / 6211 |
1 |
|
2 |
የስቴሽነሪ ዕቃዎች / 6212 |
2 |
|
3 |
የጽዳት ዕቃዎች / 6218 |
3 |
|
4 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች / 6219 |
4 |
|
5 |
የህትመት ውጤቶች / 6213 |
5 |
|
6 |
ቋሚ እቃ / 6313 |
6 |
|
7 |
የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጥገና / ፕሪንተር፤ ኮምፒውተር፤ ላፕቶፕ፤ ፎቶ ኮፒ ማሽን፤ ጄኔሬተር፤ የኔትዎርክ ዝርጋታ ሁሉም ጥገናዎች ከእነዕቃውና የእጅ ዋጋን ጨምሮ /6232 |
7 |
|
8 |
ትራንስፖርት የሚያቀርብ /አውቶብስ ወይም ሀይገር፤ የህዝብ ማመላለሻ መኪና፤ አይሱዙ የጭነት መኪና በኪሎ ሜትር/ 6232 |
8 |
|
9 |
መስተንግዶ /ቆሎ፤ ውሃ ½ ፤ ኩኪስ፤ ድፎ ዳቦ፤ የጠርሙስ ለስላሳ፤ ቦምቦሊኖ ሻይ ቡናን ጨምሮ /6271 |
9 |
|
10 |
የሰራተኛ ምገባ የሚያቀርብ ቁርስ ምሳ፤ ውሃ፤ ሻይ፤ ቡና /6221 |
10 |
|
11 |
የአትክልት ዘር፤ ዶሮ ግዥ፤ ሞራሌና ሼሬራ የሚያቀርብ /6221 |
11 |
|
12 |
የቢሮ ጥገናና እድሳት /6244 |
12 |
|
13 |
የቢሮ ኪራይ በካሬ እና የድንኳን ኪራይ /6252 |
13 |
|
14 |
የአዳራሽ ዲኮር ስራ /6253 |
14 |
በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በየሎቱ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበት ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ (ማስገባት) ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በመሙላት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ (ሲፒኦ ኮፒ ውስጥ ይግባ)
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይሞላ፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሰነዱ የመግዣ ዋጋ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ላይ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሞሉትን ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ውል በመግባት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ጽ/ቤት ታሽጎ ወዲያው 4፡30 / ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114165909/ 014703280 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቄራ ቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ ኖክ ማደያ አጠገብ።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ከሆነ አምራች ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ለሚያቀርቡት እቃዎች በሙሉ ተወዳዳሪ ነጋዴዎች የጥራት ማረጋጋጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
