Tender Detail

Tender Details


በኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ለስልጠና ለስብሰባ አገልግሎት የሚውል መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የምግብ፤ ሻይ ቡና እና መጠጥ አገልግሎት ግዥ ባለ 3 ኮከብ (ሎት 1) እና ባለ 4 (ወይም 5) ኮከብ ያላቸው ሆቴሎችን (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ኢኤአ/ባሪ/ግቢጨ/001/2018

 

በኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ለስልጠና ለስብሰባ አገልግሎት የሚውል መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የምግብ፤ ሻይ ቡና እና መጠጥ አገልግሎት ግዥ ባለ 3 ኮከብ (ሎት 1) እና ባለ 4 (ወይም 5) ኮከብ ያላቸው ሆቴሎችን (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።

በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  2. የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ በኤሌከትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ጽ/ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት የክልሉ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ወይም በካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ጨረታው ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU- ኢኤአ/ባሪ/ግቢጨ/001/2018 ሎት 1 ወይም ሎት 2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  6. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0583206999/ 0583206775 መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE