Tender Detail

Tender Details

  • Company MNS Manufacturing PLC (ኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ገጣፎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0961020160
  • Website
  • Deadline07 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-07 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (በልማት ባንክ የተወረሰ) የተለያዩ ጨርቃጨርቅና ፎጣዎችን አምራች ድርጅት ሲሆን እስከ 1,500 ለሚደርሱ ሠራተኞቻችን የምግብ አገልግሎት የሚያቀርብ ድርጅት አወዳድሮ በውድድሩ ከአሸነፈው ድርጅት ጋር ውል መያዝ ይፈልጋል፡፡

MNS Manufacturing PLC (ኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)


 

የሠራተኞች የምግብ አገልግሎት ለማቅረብ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር MNS 001/2018

 

የኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (በልማት ባንክ የተወረሰ) የተለያዩ ጨርቃጨርቅና ፎጣዎችን አምራች ድርጅት ሲሆን እስከ 1,500 ለሚደርሱ ሠራተኞቻችን የምግብ አገልግሎት የሚያቀርብ ድርጅት አወዳድሮ በውድድሩ ከአሸነፈው ድርጅት ጋር ውል መያዝ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ እየጠየቅን ለበለጠ ማብራሪያ ከታች በሚገኘው የስልክ አድራሻ በመጠየት መረዳት ይችላሉ።

 

የአገልግሎት አይነት

የጨረታው ሰነድ ግዥና መመዝገቢያ ቀን

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የፋብሪካው ሠራተኞች የምግብ አገልግሎት መስጠት

ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት

በ6ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል።

6ኛው ቀን እሁድ ወይም ሌላ በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

 

ስለሆነም-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸው ሆኖ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 ብር በኤም ኤን ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም የተዘጋጀ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ
  3. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  4. 1500,000 ብር በየስድስት ወራት የሚታደስ ቼክ ማቅረብ የሚችል፡
  5. እውቅና ካለው መስሪያ ቤት በምግብ ሥራ የምስክር ወረቀት ያለው
  6. ከዚህ በፊት ቢያንስ 6 አመት በምግብ አገልግሎት ላይ የፈረቃ ሠራተኞች ካላቸው ታዋቂ ድርጅቶች ጋር የሠራ!
  7. ከዚህ በፊት ከሠራባቸው ቦታዎች የመልካም ሥራ ምስጋና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  8. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት /VAT/ ማቅረብ የሚችል!
  9. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number/ ቁጥር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  10. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  11. ተጫራቾች በየቀኑ እስክ 1,500 ሠራተኞች መመገብ የሚችል አቅም ያላቸው፣
  12. ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ለገጣፎ ከሚገኘው ድርጅታችን ከሰው ኃብት መምሪያ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ!
  13. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ

ስ.ቁ፡- 0961020160፤ 0910744445፤ 0935403432፤ 0935986233

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE