በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ/ወ/8/ት/ጽ/ቤት የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግስት ከተመደበለት በጀት ለ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ አይነት እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።
በአ/ከ/ክ/ከ/መ/8/ት/ጽ/ቤት የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የ3ኛ ዙር የግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 003/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ/ወ/8/ት/ጽ/ቤት የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግስት ከተመደበለት በጀት ለ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ አይነት እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም፡-
ሎት 1. የቤት ውስጥ ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና (Assistive Devices መጠቀሚያ ከድምፅ ነፃ ክፍልን ማዘጋጀት) ፣
ሎት 2. የመስተንግዶ አቅርቦት
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ (ቲን ነምበር) ቁጥር ያላቸው፤
- የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ናሙና (ሳምፕል) ለሚጠይቁ እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ፤
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት1 ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ፣ ለሎት2 ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባችሁ፡፡ የጨረታ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ታሽጎ በ3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ሎት 2 የመስተንግዶ አገልግሎትን ለመስጠት ውሉ ጸንቶ የሚቆየው እስከ 6 ወር ሲሆን ከዛ በኋላ ያለው በስምምነት የሚታደስ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው
- የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት የመ/ደ/ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች/አገልግሎት ግዥ ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20 ፐርሰንት ድረስ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት አለ።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሰነድ ለምትገዙ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጃችሁ ተጫራቾች በሙሉ የጨረታ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ ደብዳቤ ታሳቢ የሚደረግላችሁ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) የሚያዝላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መሳለሚያ ወረዳ 6 ፖሊስ ጣቢያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ።
በአ/ከ/ክ/ከ/መ/8/ት/ጽ/ቤት የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
