Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ/ቅ/ጽ/ቤት ለሰራተኛ ክበብ የሚውል መገልገያ እቃዎችን እና ለሰራተኞች የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ ሀገር ውስጥ ተጫራቾችን አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥዎችን መፈፀም ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘረትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 014/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ/ቅ/ጽ/ቤት

  • ሎት 1. ለሰራተኛ ክበብ የሚውል መገልገያ እቃዎች ግዥ መለያ ቁጥር ፕሮ/ምዕራብ 014/2017
  • ሎት 2 ለሰራተኞች የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ መለያ ቁጥር ፕሮ/ምዕራብ 015/2017 በግልፅ ጨረታ ሀገር ውስጥ ተጫራቾችን አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥዎችን መፈፀም ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘረትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
  1. ተጫራቾች ለሎት1 በዘርፋ የታደሰና ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር፤ተጨማሪ እሴት ታክስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  2. ጨረታውን መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 150.00/አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አቃቂ ቃሊቲ 5000 ቤቶች ገባ ብሎ ምዕራብ/ቅ/ጽ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ከሚገኘው ጽ/ቤታችን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000.00(አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ለክበብ መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች 4:30 ሰዓት ላይ ለሰራተኞች መዝናኛ ክበብ አቅርቦት አገልግሎት 5፡00 ሰዓት የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
  5. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቁጥሩ ሊጨምር ሊቀንስ ይችላል።

አድራሻ:- አቃቂ ቃሊቲ 5000 ቤቶች ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር:- 0940 284 224 ወይም 0931 804 871

 

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE