የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የቀላል ተሸከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PMO/NCB/20/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የቀላል ተሸከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በኢፊዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 ብር 90,000.00 (ዘጠና ሺ ብር) እና ለሎት 02 ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PMO ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/NCB/20/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6:00 ከ ሰዓት 7፡00 -11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 መመልከት ይቻላል ።
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-1-26-31-53 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
