Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ሎት -2- አላቂ የመኪና እቃዎች፣ሎት 3 ሌሎች የመኪና እቃዎች ሎት 4 የጥርሳ ጥርስ ዘይትና ቅባቶች ሎት 5 የእንስሳት መድሀኒት ሎት 6 አመታዊ የመኪና ጥገና ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ሎት -2- አላቂ የመኪና እቃዎች፣ሎት 3 ሌሎች የመኪና እቃዎች ሎት 4 የጥርሳ ጥርስ ዘይትና ቅባቶች ሎት 5 የእንስሳት መድሀኒት ሎት 6 አመታዊ የመኪና ጥገና ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. የጨረታ መለያ ቁጥር-ቃ/ወ/ግ/ጨ/01/2019
  2. ተጫራቾች ኦርጂናል የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና እንድሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ማቅረብ ሲጠበቅባቸው የመረጃዎቹ የማይመለስ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ይኖርበታል።
  3. ሎት 6 ጋራዥን በተመለከተ አሸናፊው ድርጅት ኮምቦልቻ ከተማ ላይ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት ከሎ1ት እስከ የተጠቀሱትሎቶች ያሉትን እቃዎች በተመለከተ ቢሮአችን በሚገኝበት ኮ/ቻ ከተማ ድረስ መቅረብ ሲኖርባቸው እቃዎቹን ንብረት ክፍል ድረስ መቅረብ ሲኖርባቸው እቃዎቹን ንብረት ከፍል የማስገባትና እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍነው አቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  4. ማንኛውም ተጫራች ግብር የከፈሉበትን ህጋዊ መረጃ ማቅረብ አለበት።
  5. የሚፈለገውን የእቃና አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ05/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 14/01/2019 ዓ/ም 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመከፈል መግዛት ትችላላችሁ።
  7. ለእቃ ግዥ ከብር 20,000 በላይና ለአገልግሎት ግዥ ከብር 10,000 ብር በላይ ዋጋ ከተሞላ ከሚከፈለው ከፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑ ይታወቅ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሞላውን ዋጋ ብዜት ወደ ጎን እንድሁም ጠቅላላ ድምሩን ወደታች ካላስቀመጠ፤ በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዘ ድልዝ ካለና በንባብ በተሰማው ጠቅላላ ዋጋና በሚመለከተው አካል ተስልቶ በሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ መካከል ከ3% በላይ ልዩነት ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለ73 ሰባ ሶስት ተከታታይ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን የመጫረቻ ሰነዱ ደግሞ ጨረታው ከሚከፈትበት እለት ጀምሮ ለ45 አርባ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
  10. ተጫራቾች ለሎት 1 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፤ለሎት-2- 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፤ ለሎት3 10,000 አስር ሺህ ብር ፤ ለሎት –4- 10,000 አስር ሺህ ብር፣ ለሎት-5 8,000/ስምንት ሺህ ብር ፣ለሎት- 6- 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። የሚያስይዙት የጨረታ ማሰከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ73 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።
  11. የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከሎት1 እስከ 5 ላሉት ሎቶች የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ እንድሁም ለሎት 6 – 3% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ግዴታ ነው።
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ ቤት ግን አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን 15/01/2019 ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚችል ሲሆን በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት ኢያግደውም።
  13. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበኣል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰኣት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰኣት ይከፈታል።
  14. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ድምር ነው።
  15. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
  16. በሎት 5 የተጠቀሱት የእንስሳት መድሀኒቶች የቆይታ ጊዜያቸው ከ2 አመት የሚያንስ መሆን የለበትም
  17. አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጂናል እቃዎችን ማቅረቡ ግዴታ ሲሆን ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ ጽ/ቤታችን ያዘጋጃቸውን ናሙናዎች በማየት በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  18. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  20. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 551 4657/033 551 4644 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ኮምቦልቻ

✨ messages.ai_summary
Supply of vehicle tires, consumable and other vehicle parts, oils and lubricants, veterinary medicines, and annual vehicle garage services for sector offices in Kalu Woreda, South Wollo Zone. Bidders must meet licensing, tax, and VAT registration requirements.
Save Tender