በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊከ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003 2017
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊከ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎቱ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የሰራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት |
10,000 |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ ማቅረብ አለባቸው።
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ደብዳቤ እንዲሁም ክሊራንስ / ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. /CPO/ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለጠቅላላ ሰነድ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ፐብሊክ ሰርቪስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት አያት ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ኢንጆይ ሞል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስ ፑል አስ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አንደኛው (11ኛው) የስራ ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የስራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከ ጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፐብሊክ ሰርቪስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን አያት ለሚኩራ ክ/ከተማ ኢንጆይ ሞል 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ከአጠቃላይ ግምት ዋጋ 10% የውል ማስረከቢያ በማስያዝና ከቡድኑ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- ተጫራቾች የውሃ የመብራት ፍጆታዎች በመስሪያ ቤቱ የሚሸፈን መሆኑን አውቃችሁ ለሰራተኛው የምትሞሉትን የምግብ፣ የለስላሳና ሻይ ቡና ዋጋ ላይ በአነስተኛ እና በጥራት እንደምትሰሩ ማወቅ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ለሚኩሪ ክ/ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ 0118593906 በስራ ሰዓት ይደውሉ
- ሲፒኦ ሲዘጋጅ ለ/ኩ/ክ/ከተማ አስ/ፐ/ሰ/የሰ/ሃ/ል/ፑል አስ/ፋ/ጽ/ቤት
(L.K.S.C.P.S.H.R.D.POOL AD&Fi.Office)
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
