የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በካራቆራ ዕቃ ግምጃ ቤት እና በክልል አ/አ/ኤ/አ ዕቃ ግምጃ ቤቶች አገልግሎት መስጠት የማይችሉትን የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን ፤ ጎማዎችን ባዶ በርሜሎችን እና የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/NCB/19/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በካራቆራ ዕቃ ግምጃ ቤት እና በክልል አ/አ/ኤ/አ ዕቃ ግምጃ ቤቶች አገልግሎት መስጠት የማይችሉትን የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን ፤ ጎማዎችን ባዶ በርሜሎችን እና የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ፡-
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ ፕሮጀክት ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/NCB/19/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀከቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ነው በመቅረብ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎች በሚገኙበት ዕቃ ግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም⁄ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ይመልከቱ ፡፡
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0111275503 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
