አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ በሎት 1 : ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ኪራይ አገልግሎት ሎት2፡-የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ተሳኮ/ፋኦ/001/2017/2025
- አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ በሎት 1 : ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ኪራይ አገልግሎት ሎት2፡-የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ከላይ የተጠቀሰውን በሎት 1- ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ አገልግሎት ኪራይ ሎት 2፡-የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቶች ታሽጎ ማህተም ባለው ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ።
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥት ጨረታ አዋጅ በተገለጸው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት በሎት 1- ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ : አገልግሎት ኪራይ በሎት 2፦የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት የሚከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች ሆኖ :-
- ከስራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽና በማንኛውም የመንግስት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ከገቢዎችና ጉምሩክ የተሰጠ ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax clearance)
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ
- የተፈረመ እና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በሎት 1: ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ አገልግሎት ኪራይ በሎት 2፡-የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በቁጥር 8 “ለ” በተገለጸው አድራሻ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ። ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጣቸውን ደብዳቤ በማቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8 ለ በተገለጸው አድራሻ በሎት :: ለኮሌጁ ማህበረሰብ የሻይና የጀበና ቡና እንዲሁም የቁርስ : አገልግሎት ኪራይ : በሎት 2፦ የተማሪዎች መዝናኛ ሻይ ቤት ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ሚያዝያ 16 ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ወይም ከዚህ ቀን በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ፦ ሎት1:- 7,000.00/ ሰባት ሺ ብር /በ ሎት2 ፡-15,000 /አስራ አምስት ሺ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ ሆኖ ለሶስት ወር የሚቆይ የባንክ ዋስትና አያይዘው ያቀርባሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8 “ሐ” በተገለጸው አድራሻ ሚያዝያ 16 ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
ሀ/ ሰነዶቹ የወጣበት አድራሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1
ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሣይንስ ኮሌጅ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር +251111223615
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ
