Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል
  • Address , Phone: 0919373502
  • Website
  • Deadline16 Mar 2025, 3:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል ለውስጥ ሠራተኞች አና ለሰልጣኞች የሚቀርብ የምግብ እና የሪፍሬሽመንት አገልግሎት ለመግዛት እና ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ካፊቴሪያ ለማከራየት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል


የጨረታ ማስታወቂያ 001/2017

 

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል ለውስጥ ሠራተኞች አና ለሰልጣኞች የሚቀርብ የምግብ እና የሪፍሬሽመንት አገልግሎት ለመግዛት እና ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ካፊቴሪያ ለማከራየት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 00 (ሁለት መቶ)በመክፈል አዳማ በሚገኘው በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በማያያዝ የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ጨረታው ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 9፡00 (ዘጠኝ ሰዓት) ድረስ አዳማ በሚገኘው የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ 9፡00 (ዘጠኝ ሰዓት) ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 9፡30 (ዘጠኝ ተኩል)በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል አዳራሽ ይከፈታል።
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በካላንደር የሚዘጉ የበአላት ቀን ወይም የዕረፍት ቀን ቢሆን የጨረታው መክፈቻው ቀን በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስረከቡበትን ድምር ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) የጨረታ ዋስትና (Bid bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ስራ የሚያከናውኑበት የውል ማስከበሪያ ወይም የመልካም ሥራ ዋስትና ድምር ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በኦሮሚያ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል ጋር ውል ይፈራረማሉ።
  8. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ሰነድ ተመርምሮ አሸናፊው እንደታወቀ ይመለስላቸዋል።
  9. የምግብና የመጠጥ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ አዳማ ከተማ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥናት ስልጠና ማዕከል ግቢ ውስጥ ነው።
  10. የኦሮሚያ የትምህርት ጥናትና ስልጠና ማዕከል የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 19 37 35 02 መደወል ይችላሉ።

 

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት

ጥናትና ስልጠና ማዕከል

 

Save Tender