የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅጥር ጊቢው ውስጥ የሚገኘውን የሰራተኞች ክበብ (ካፍቴሪያ) በዘርፉ ልምድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሶስተኛ ወገን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ም/አ/አ/ሪጅ/ግ/ጨ/003/2017 (ሎት-3)
የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅጥር ጊቢው ውስጥ የሚገኘውን የሰራተኞች ክበብ (ካፍቴሪያ) በዘርፉ ልምድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሶስተኛ ወገን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎቱ ዓይነት |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
1 |
የሰራተኞች ክበብ (ካፍቴሪያ) አገልግሎት |
ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ብር 10000.00 (አስር ሺህ) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያለው እና የግብር መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-EAAD AACC (1000298392902) ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በማድረገ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » እና ፋይናንሻል «አሪጅናል እና ኮፒ » በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ቁጥር EEU/EAAR/NCB/003/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የምስራቅ አዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰፕላይ ቼይን ግዥ፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር +251-011-67-32-353 መደወል ይችላሉ፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
