በአራዳ ከ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2017 በጀት ዓመት ለሻይ ከበብ የሚያስፈልገው የምግብ ፣ የትኩስ እና ቀዝቃዛ መጠጥ አገልግሎት ለሚያቀርብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የሻይ ክበብ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በአራዳ ከ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2017 በጀት ዓመት ለሻይ ከበብ የሚያስፈልገው የምግብ ፣ የትኩስ እና ቀዝቃዛ መጠጥ አገልግሎት ለሚያቀርብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማስረጃ ያላቸው TIN NO የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እና የገቢዎች ክሊራንስ ግዜው ያላለፈበት ደብዳቤ ያላቸው::
- ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እና በመንግስት ግዥ ያልታገዱ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በፖስታ አሽገው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር 5000.00 (አምስት ሺ ብር) በኢትጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ) ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር ) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል ኦርጂናል እና እንዲሁም የቴክኒካል የኦርጅናል ኮፒ በመለየት ተሟልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሽግ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ አድራሻ ተጽፎ ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ት/ቤቱ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅፅ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 (አራት ተኩል ) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እለቱ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የሻይ ከበቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታውን ሰነድ በነፃ ይወስዳሉ ከአደራጃቸው ተቋም ወቅታዊ የሆነ በአድራሻችን የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ መስሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ :- አራት ኪሎ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎን ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡
ዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
የት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ስ.ቁ 011-23-28-66
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣
አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
