Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
  • Address ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-26-31-53
  • Website
  • Deadline02 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Vehicle tire

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ::


የጨረታ ማስታወቂያ

 ጨረታ  ቁጥር  EEU/PMO/NCB/12/2017

 

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት /ቤት የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ::

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ፣በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  2. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ... ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት /ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንጻ ላይ 11 ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኃላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PMO ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/PMO/ NCB/12/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ህዳር 23 ቀን 2017 . እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በኢ... ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት /ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ 11 ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ህዳር 23 ቀን 2017 . ቀኑ 830 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200-600 ከሰዓት 700 -1100 እና ቅዳሜ ጠዋት 200 – 600 መመልከት ይቻላል
  7. የፕሮግራም /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-1-26-31-53 መደወል ይችላሉ፡

 

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት

Save Tender