Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline16 Dec 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዢ ሎት 1- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 2- የሞተር ሳይክል ግዥ፣ ሎት 3- የጭነት አገልግሎት፣ ሎት 4- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 5- የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዢ ሎት 1- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 2- የሞተር ሳይክል ግዥ፣ ሎት 3- የጭነት አገልግሎት፣ ሎት 4- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 5- የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ለሎት 1 እና 3 በተሰማሩበት ዘርፍ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት የዘመኑን የቴክኒክ ምርመራ አልፎ ቦሎ ያለው፣ የተሟላ የመድን ሽፋን ዋስትና ያለው እንዲሁም የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ለሎት 1፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ሃምሳ ሺህ ብር (ብር 50,000)

ሎት 2፡- የሞተር ሳይክል ግዥ ሃምሳ ሺህ ብር (ብር 50,000)፣

ሎት 3፡- የጭነት አገልግሎት አርባ ሺህ ብር (ብር 40,000)፣

ሎት 4፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ሰላሳ ሺህ ብር (ብር 30,000)፣

ሎት 5፡- የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አንድ መቶ ሺህ ብር (ብር 100,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ለሎት 5፦ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
  3. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  4. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር  0471355629  የቤንች  ሸኮ  ዞን  ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ  ሚዛን  አማን

 

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ

እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

Save Tender