የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውል መዝናኛ ክበቡን ኮንትራት ወስደው የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚያቀርቡ ግለሰቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
ለሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ከ/አስተ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/
ጨ/ቁ/09/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውል መዝናኛ ክበቡን ኮንትራት ወስደው የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚያቀርቡ ግለሰቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
- በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ድርጅቶች ግለሰቦች፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በክበብ አገልግሎት ልምድና ፍላጐት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አሥር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.አ. ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የ90 ቀን /Unconditional/ ቢድ ቦንድ ጋራንቲ ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 በቢሮው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊትለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና CCRDA መካከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0114-621457/0911060918
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን
ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት
